Skip to Content

Happy new Year 2007

ጡረተኞች በተደረገው የደሞዝ ማስተካከያና ጭማሬ መደሰታቸውን ገለጹ

መንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በ2006 በጀት ዕቅድ አፈጻጸም ዋና ዋና ጉዳዮች እንዲሁም የጡረታ አበል ጭማሪና ማስተካከያን አስመልከቶ ከህዝብ ክንፍ አባላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ የቪዲዮ ኮንፍረንስ አካሄደ፡፡

ለዝርዝሩ ይህን ይጫኑ

ለዋና ባለመብቶች የሚደረግ የአበል ማሻሻያ የጭማሪ አሰራር

ለጡረተኞች የጡረታ አበል ጭማሪና ማስተካከያ ተደረገ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ለጡረተኞች የጡረታ አበል ጭማሪና ማስተካከያ መደረጉን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳባ ኦርያ በዋናው መስሪያቤት ነሐሴ 2 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ የዜጎችን የማህበራዊ ዋስትና የማረጋገጥ መርህ ተግባራዊ በማድረግ፤ የድህነት ቅነሳ ፕሮግራምን ለማሳካት ዝቅተኛ የጡረታ አበል ተከፋይ ባለመብቶችን ኑሮ ለመደጎም እና ጡረተኞችን ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት ለመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ማድረጉን ተከትሎ ለጡረተኞችም የጡረታ አበል ጭማሪና ማስተካከያ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ለዝርዝሩ ይህን ይጫኑ

የኤጀንሲው አመራሮች እና ሠራተኞች በሰንዳፋ አካባቢ የችግኝ ተከላ አከናወኑ፡፡

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አመራሮች እና ሠራተኞች ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰንዳፋ አካባቢ በሚገኘው የችግኝ መትከያ ቦታ ላይ የችግኝ ተከላ አከናወኑ፡፡

በዕለቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ አቶ አያሌው ዱሬሳ እንዳሉት ተቋሙ በአገር ልማት እና እየታየ ባለው የአየር ለውጥ ላይ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማድረግ በተራቆቱ አካባቢዎች ላይ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የሚያከናውን መሆኑን ገልጸው ይህም ቀጣይነት ያለውና ኤጀንሲው በዕቅዱ አካቶ እየሰራበት የሚገኝ የአካባቢ እንክብካቤ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ ይህን ይጫኑ

የዜጎች ቻርተር

መረጃዎትን ያረጋግጡ

እባክዎ የጡረተኛ መለያ ቁጥር ያስገቡ!