በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቅጥር ግቢ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ — የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሠራተኞች መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል በማስመልከት፣ በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሰፊ የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።

ይህ የጽዳት ዘመቻ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተጀመረውን የጽዳትና ውበት መርሃ ግብር መነሻ ያደረገ ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም የተቋሙን ቅጥር ግቢና አካባቢውን ጽዱ፣ ሳቢና ለሥራ ምቹ ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአዲሱ ዓመት በሠራተኞች ዘንድ አዲስ የሥራ መነሳሳትና መነቃቃትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በዕለቱ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ ከተቋሙ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ሠራተኞች ተሳትፈውበታል።

Share this Post