About

There are two institutions that provide social security services in Ethiopia, one of which is the Government Employees Social Security Agency. The agency is a federal government office established by Council of Ministers Regulation No. 203/2003 to implement the Government Employees Pension Proclamation. 

Mission

የአገልግሎትን አሰጣጥን በማዘመን የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ !

Vision

በ 2022 ጡረታ እቅድ የተሸፈኑ ዜጎች ፍትሀዊ የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ማየት !

Goals

   የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ !

Core Values

          * ተገልጋዮች የህልውናችን መሰረቶች ናቸው !

          * የጡረተኞችን ህይወት ለመለወጥ እንተጋለን

          * በቡድን ውጤት እናምናለን

          * ሙስናና አድልዎን እንጠየፋለን

          * በአክብሮት እናገለግላለን

Duties & Responsibilities

የመንግስት ሠራኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 203/2003 . አንቀፅ አምስት መሰረት ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡-

  •  የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በስራ ላይ ያውላል፤
  • የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድን ለማስፈፀም ቀልጣፋና ብቃት ያለው አሰራር ይዘረጋል፣ ይተገብራል፤
  • የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ መዋጮ አሰባሰብ ሥርዓት ይዘረጋል፣ መዋጮ ይሰበስባል፣ በሚመለከተው የመንግስት አካል በኩል በተገቢው ጊዜና መጠን መሰብሰቡን ያረጋግጣል፣ አሠሪ መሥሪያ ቤቶች ሥርዓቱን ተግባራዊ ማድረጋቸውን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ ሲሆን ሰነዶችንና መዛግብትን አስቀርቦ ወይም በአሠሪ መሥሪያ ቤቶች ተገኝቶ ይመረምራል፤
  • የመንግስት ሠራኞች ጡረታ ፈንዶችንና ከፈንዶቹ ጋር የተያያዙ ሀብቶችን ያስተዳድራል፤
  • የመንግስት ሠራተኞችን ለጡረታ መብት ብቁ የሚያደርግ ማስረጃዎችን በቅድሚያ አሰባስቦ ይይዛል፤
  • የጡረታ መዋጮ በወቅቱ በማይከፍሉ፣ የጡረታ መዋጮ ሂሳብ መዝገብ በማይዙ፣ ማስረጃ በማይልኩ እና መረጃ በማይሰጡ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና ግለሰቦች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
  •  የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ መብት ለማስከብር የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ብቃት እና ተቀባይነት፣ የጥቅም ዓይነት እና መጠኑን ይወስናል፣ ክፍያ ይፈፅማል፤
  • የመንግስት ሠራኞች ጡረታ መብትና ጥቅም ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፤
  • የመንግስት ሠራኞች ጡረታ ፈንዶችን በትሬዠሪ ቦንድና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ በሚወሰኑ ትርፋማና አስተማማኝ በሆኑ ሌሎች ኢንቨስትመንቶች ላይ ያውላል፤
  • የመንግስት ሠራኞች ጡረታ ፈንዶችን በየተወሰነ ጊዜ በሂሳብ ስሌት አዋቂዎች እንዲጠኑ ያደርጋል፤
  • የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ ፕሮግራሞች ስለሚጠናከሩበት ሁኔታ ጥናት እያካሄደ ለመንግስት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • በሥልጣንና ተግባሩ ሥር የተመለከቱ ጉዳዮችን በሚመለከት መመሪያዎችን ያወጣል፤
  • የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
  • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
  • ሥልጣንና ተግባሩ ሥር የተመለከቱ ጉዳዮችን በሚመለከት መመሪያዎችን ያወጣል፤
  • የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
  •  ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡