በአንድነት ፓርክ የጉብኝት መርሃ ግብር ተካሄደ

በአንድነት ፓርክ የጉብኝት መርሃ ግብር ተካሄደ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች ነሐሴ 17/2015 የአንድነት ፓርክን ጎበኙ፡፡

በዕለቱም በታሪካዊው የብሔራዊ ቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ1880ዎቹ ጀምሮ የተገነቡ እና ቀድሞ የነበሩበትን ይዞታ ሳይለቁ በተለያዩ ጊዜያት እድሳት የተደረገላቸው የነገስታት መኖሪያና ፅህፈት ቤቶች፣ የአጤ ሚኒሊክ መኝታ ቤት፣ ፀሎት ቤት፣ የልዑላን የመኝታ ክፍል፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል መኝታ ቤትና የተለያየ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሌሎች ክፍሎች በውስጡ የሚገኙበት እንቁላል ቤት በሚል የሚጠራውና በአብዛኛው ከእንጨት የተሰራው ባለ አንድ ፎቅ ቤት የተጎበኘ ሲሆን፣ የመመገቢያ አዳራሽ የነበረውና ታላላቅ ሀገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ሁነቶች የተካሄዱበት የሚኒሊክ የግብር አዳራሽ፣ የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት 2ኛ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ቻርልስ ደጎል፣ የዩጎዝላቪያው ፕሬዚዳንት ቲቶ እና ሌሎችም የውጪ ሀገራት እንግዶች የተስተናገዱበት ህንጻ እንዲሁም በደርግ ዘመነ መንግስት የአጼ ኃይለስላሴ ባለስልጣናት ታስረው የተሰቃዩበት ምድር ቤት የጉብኝቱ አካል ነበሩ፡፡ በተጨማሪም የእንስሳት ማቆያ እና አኳሪየም/የዓሣ ገንዳ/፣ የብሔር ብሔረሰቦች ባህል የሚታይበት ቦታ እና ሌሎችም በፓርኩ የሚገኙ ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህቦች ተጎብኝተዋል፡፡

በተያያዘም አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ ያስገነባውና ለተለያዩ የንግድ አገልግሎቶች የሚውለው ዋስትና ሕንጻም ነሐሴ 18/2015 ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

በአንድነት ፓርክ እና በዋስትና ሕንጻ በተካሄደው የጉብኝት መርሃ ግብር የተቋሙን አመራሮች ጨምሮ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ከዋናው መ/ቤት፣ ከሪጅንና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የመጡ የስራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል፡፡

Share this Post