የአስተዳደሩ ሠራተኞች የአብሮነት ጉዞ አካሄዱ

የአስተዳደሩ ሠራተኞች የአብሮነት ጉዞ አካሄዱ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሠራተኞች ጳጉሜ 6 ቀን 2015 በአብሮነት ቀን መነሻቸውን ዋናው መ/ቤት በማድረግ ፒያሳ የሚገኘው የአስተዳደሩ ዋስትና ሕንፃ ድረስ የደርሶ መልስ የአብሮነት ጉዞ አከናወኑ።

የጉዞው ዋና ዓላማ የኢትዮጵያውያንን የአብሮነት ዕሴቶች በመጠቀም እየተፈታተኑን ያሉ ችግሮችን በይቅርታ በመሻገር አዲሱ ዓመት የሕዝቦች አብሮነት የሚጠናከርበት እና የመልካም አዲስ ዘመን ምኞት እንዲለዋወጡበት ማድረግ ነው።

የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ በጉዞው ወቅት እንዳሉት ዓመቱ አስተዳደሩ ዕቅዶቹን ያሳካበት እና ተቋማዊ ሪፎርም ያካሄደበት በመሆኑ ውጤት የተመዘገበበት ነው ብለዋል።

በዚህ የአብሮነት ጉዞ የአስተዳደሩ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

 

Share this Post