አስተዳደሩ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

አስተዳደሩ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከጥር 6 እስከ 7/2016 በዋናው መስሪያ ቤት ገመገመ።

በመድረኩ ላይ በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው አስተዳደሩ ባለፉት ስድስት ወራት በሥራ ላይ ለሚገኙ 75,470 ሠራተኞች የጡረታ መለያ ቁጥር የመስጠት፣ ለ33,344 አዲስ የጡረታ ባለመብቶች የጡረታ አበል የመወሰን፣ የጡረታ አበል ክፍያን በተጨማሪ አምስት ባንኮች የመፈጸም፣ ብር 23.37 ቢሊየን የጡረታ መዋጮ ገቢ የመሰብሰብ፣ ከ1,290 የመንግስት መ/ቤቶች ለተሳተፉ 3,561 የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የመሰጠት፣ ለ1,812 የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የተለያዩ የአቅም ማሳደጊያ ስልጠና የመስጠት፣ በአሠሪ መ/ቤቶች በመገኘት የጡረታ መዋጮ ገቢ ምርመራ የማካሄድ ስራዎች ተከናውነዋል የተባለ ሲሆን፣ ለአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ችግኝ የመትከል፣ የደም ልገሳ እና ሠራተኞች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምርመራ እንዲያካሄዱ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

የጡረታ አበል ክፍያ ሂሳብ ማወራረድ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን፣ የኦዲት እና ቁጥጥር ስራዎች አነስተኛ መሆን እንዲሁም የሰው ኃይል ቅጥር በዕቅዱ መሰረት አለመከናወኑ በሪፖርቱ በድክመት የተነሱ ሲሆን፣ በአጠቃላይ አስተዳደሩ በግማሽ ዓመቱ የዕቅዱን 87 ከመቶ አከናውኗል ተብሏል።

ለሁለት ቀናት በዋናው መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚህ የዕቅድ አፈጻጸም መድረክ ላይ የተቋሙ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች እና የሪጅን ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች ተካፍለዋል፣

Share this Post