የአቅም ውስንነት ያለባቸው አረጋዊያን መኖሪያ ቤት የሚሆን ህንጻ ለመገንባት የግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ተከናወነ

የአቅም ውስንነት ያለባቸው አረጋዊያን መኖሪያ ቤት የሚሆን ህንጻ ለመገንባት የግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ተከናወነ

========//=======

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በባህር ዳር ከተማ ለ14 የአቅም ውስንነት ያለባቸው አረጋዊያን አባወራዎች የሚሆን መኖሪያ ቤት ለመገንባት ግንቦት 22/2017 ዓ.ም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ሠራተኞች እና በባህር ዳር ከተማ የጣና ክ/ከተማ አስተዳደር ተወካዮች በተገኙበት የግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ተከናወነ።

 

የሚገነባውን የህንጻ ዲዛይን የሰራው ዱነያ አማካሪ መሐንዲሶች ሲሆን ለግንባታዉ ጥላሁን አበበ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ቃል የገባ መሆኑን ተመላክተዋል ።

 

አስተዳደሩ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በይርጋለም ከተማ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ በሚገመት ወጪ ለ8 የአቅም ውስንነት ላለባቸው ጡረተኞችና ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በማስገንባት ማሰረከቡን የሚታወስ ነው።

 

//****

ግንቦት 25/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

Share this Post