የሌማት ትሩፋ ፕሮጀክት ለመተግበር የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
የሌማት ትሩፋ ፕሮጀክት ለመተግበር የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
==========//=======
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ዳባ ኦርያ በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ በቱሉ ዲምቱ ቁጥር 2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚተገበር የሌማት ትሩፋት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም የሸገር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኮዬ ፈጨ ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ አጋር አካላቶች እና የአስተዳደሩ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም የትምህርት ቤቱ አመራሮች እና መምህራኖች በተገኙበት አኖሩ፡፡
ይህ የሚተገበረው የሌማት ትሩፋት ፕሮጀክት ከ8-10 የተሻለ ዝርያ ያላቸዉ የወተት ላሞች እና ከ500 በላይ የሚሆን የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች የማርባትን ስራ መነሻ በማድረግ የሚጀመር ሲሆን ፕሮጀክቱ የተማሪዎችን ምገባ እና ገቢያቸው ከደህነት ወለል በታች ለሚገኙ የጡረታ ባለመብቶችን የምግብ አቅርቦትን እንዲሁም ኑሮ ለማሻሻል እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት የሚያስችል መሆኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ፋይናንስን በሚመለከት የእንስሳት እና የእንስሳትና መኖ ግዥ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቱን ለመጀመር የሚያስፈልገው ወጪ አቢስንያ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ፣ ሕብረት ባንክ፣ ኦሮሚያ ባንክ እና አባይ ባንክ የሚሸፍኑ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡ የግንባታ ሥራዎችን በሚመለከት አሴፍ ኢንጂነሪንግ ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ እንደሚገነቡ ቃል ገብተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና የ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመር መረሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን ከ500 በላይ የሚሆኑ ለምግብነት የሚያገለግሉ እንደ አቡካዶ፣ ማንጎ እና ሌሎች ችግኞች በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተተክለዋል፡፡
አስተዳደሩ ለበርካታ ተከታታይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎችን እያከናወነ መቆየቱን እና የአቅም ውስንነት ላለባቸው ዜጎች አጋር አካላትን በማስተባበር የመኖሪያ ቤቶችን እድሳት እና በተለይ በሲዳማ ክልል በይርጋለም ከተማ ለ8 አባወራዎች በማስገንባት ማሰረከቡ ይታወሳል።
://****
ሰኔ 13/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ