በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ

በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች 7ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በጅማ ከተማ መንቲና ወረዳ አካሄዱ።

ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 700ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር በመትከል እንደ ሃገር የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የተካሄደ ነው።

በተያያዘም የዋናው መ/ቤት ሠራተኞች በሸገር ከተማ በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ቀርሳ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ያካሄዱ ሲሆን፣ የአስተዳደሩ ሁሉም ሪጅን እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችም በያሉበት አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ያከናወኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

Share this Post