አስተዳደሩ ለሠራተኞቹ ምስጋና አቀረበ
አስተዳደሩ ለሠራተኞቹ ምስጋና አቀረበ
===========//==========
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ላስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ምስጋና አቅርቧል።
ሐምሌ 28/2017 በዋናው መ/ቤት በተካሄደው የምስጋና መርሃ ግብር ላይ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ የዕቅዱን 95 በመቶ ማከናወኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ስኬትም ከዋና መ/ቤት እስከ መስክ ጽ/ቤቶች ድረስ ያሉ የአስተዳደሩ ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው የተገኘ ነው ተብሏል።
ይህ የምስጋና መርሃ ግብር ‘የሠራተኞች የምስጋና ቀን’ በሚል በየዓመቱ በአስተዳደሩ የሚካሄድ ሲሆን፣ የሠራተኞችን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ስራቸውን በመግባባትና በቀና መንፈስ እንዲያከናውኑ የሚያግዝ መሆኑንም ተገልጿል።
በመረሃ ግብሩ አስተዳደሩን ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተው በጡረታ ለተሸኙ ሠራተኞች ምስጋና እና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
://****
ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ