በውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት እና ምዘና ስርዓት መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ

በውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት እና ምዘና ስርዓት መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ

                    ========##==========

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ በተዘጋጀው የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት እና ምዘና ስርዓት መመሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች የካቲት 11/2018 ስልጠና ሰጠ።

 

አዲስ የተዘጋጀውን የምዘና ስርዓት አስመልክቶ በተዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን በቀለ እንዳሉት አስተዳደሩ ሪፎርሙን ተግባራዊ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች ማምጣት ቢችልም ውጤቶቹን እና የተቋሙን አፈጻጸም መለካት ላይ ግን ክፍተቶች ይታያሉ ብለዋል። ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው የክትትል ማነስ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህንን እና ሌሎች የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተዘጋጀው አዲስ የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት እና ምዘና ስርዓት በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ ይደረጋል።

 

መመሪያው የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ሠራተኞች ለመለየትና በተሰራው ስራ ልክ ውጤት እንዲያዝ ያስችላል። በተጨማሪም ጤናማ የሆነ የውድድር መንፈስ እንዲኖር የሚያደርግ ሲሆን፣ ስልጠናውም ሁሉንም የስራ ኃላፊዎች ወደ ተመጣጣኝ ደረጃ እንዲመጡ ያግዘል ብለዋል።

 

ሰልጠናው በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተሰጠ ሲሆን፣ በቅርንጫፍና በሪጅን ጽ/ቤቶች፣ እንዲሁም በዋናው መ/ቤት ከቡድን መሪ በላይ ያሉ የስራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል።

Share this Post