ኑ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ ተካሄደ

ኑ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ ተካሄደ
==============//==============
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. “ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ 8ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዱ።
 
በአራት ኪሎ በሚገኘው ግንፍሌ ፓርክ በተከናወነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም የመሃል ሪጅን ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በጋራ በመሆን የፍራፍሬና የተለያዩ ዓይነት የዕፅዋት ችግኞችን በጋራ ተክለዋል።
 
በዕለቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሸጉ ኬሎ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረትን መለዋወጥ ከመጠበቅ ባሻገር ሀገራችን በምግብ ራሷን እንድትችል የሚደረገውን ዘላቂ ጥረት በእጅጉ የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም “ችግኝ መትከል ልማትን መትከል ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ሁላችንም የተከልነውን ችግኝ በአግባቡ በመንከባከብና በማሳደግ ረገድ የድርሻችንን መወጣት እንዳለብን አሳስበዋል።
 
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የችግኝ ተከላ እና የእንክብካቤ ሥራዎችን በዓመታዊ ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ውስጥ አካቶ በየዓመቱ በኃላፊነት ስሜት የሚያከናውን ሲሆን፣ ዘንድሮም ያስጀመረውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተጠናከረ የችግኝ ተከላ እና የእንክብካቤ ሥራዎች ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል።

Share this Post