የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮች እና ሠራተኞች “የመጋቢት 24 ፍሬዎችና ቀጣይ የሀገራችን ተስፋዎች” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አደረጉ

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር  አመራሮች እና ሠራተኞች “የመጋቢት 24 ፍሬዎችና ቀጣይ የሀገራችን ተስፋዎች” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት አደረጉ

==========//============

የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር አመራሮች እና ሠራተኞች “የመጋቢት 24 ፍሬዎችና ቀጣይ የሀገራችን ተስፋዎች” በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 22/2017 ዓ/ም ውይይት አድርገዋል።

 

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳባ ኦርያ ሲሆን እንደ እሳቸው ገለጻ የለውጡ መንግስት ከመጋቢት 24/2010 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ውስብስብ ፈተናዎችን እየተጋፈጠ አኩሪና እምርታዊ ድሎች እያስመዘገበ ለህዝቡ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወደፊት እየሄደ ያለ መንግስት በመሆኑ የመጋቢት ውጤቶችን ለሠራተኞች ግንዛቤ በመፍጠር የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል የታለማ መድረክ መሆኑ ገልጿል።

 

እንደሳቸው ገለጻ በሀገራችን የቆየውን ውስብስብ ችግሮችን ግምት ውስጥ ያስገባ አሁን የሚንገኝበትን አለም አቀፋዊ ሁኔታን በመለየት ወደፊት የሚሄድ መንገድና አቅጣጫ የያዘ ስርዓት መሆኑን ሰራተኛው ጠንቅቆ በመረዳት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም አንስቷል።

 

ከዚህ በተጨማሪ ለውይይት የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን ቀኑ ብልፅግና ፓርቲ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ በርካታ ተግባራት ተሰርተው ውጤትም አይተናል እንደ ሃገር የለውጡ የብልፅግና ፣ የሃገር በቀለ እሳቤ መጀመሪያ በመሆኑ በልዩነት ልናስበው እና ልንተገብረው ይገባል ብለዋል።

 

በመጨረሻም  ለውጡን አጠናክሮ በማስፋትና ዘላቂነቱን በማረጋገጥ የዜጎችን ህይወት በሁለንተናዊ መልኩ ለመለወጥና የሀገራችንን እና የዜጎቻችን ህልምና ርዕይ ለማሳካት እኛ የአስተዳደሩ ሠራተኞች መልካም ስኬቶቻችንን እያስቀጠልን፣ ጉድለቶቻችንን እያረምን በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት ማስቀጠል እንዳለብን ተገልፆ መድረኩ ተጠናቋል ። በውይይት መድረኩ ላይ የመሃል ሪጅን ሃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

 

ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!

 

//****

መጋቢት 23/2017 ዓ/ም

አዲስ አበባ

Share this Post